የጥራት መንደር አመራሮችና ሠራተኞች የፅናት ቀንን አከበሩ፡፡
የጥራት መንደር አመራሮችና ሠራተኞች የፅናት ቀንን አከበሩ፡፡
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም ኢሥኢ
የጥራት መንደር አመራሮችና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ታስቦ የሚውለውን የፅናት ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል አክብረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ እንዳሉት የቀደሙት እናት አባቶቻችን በነበራቸው ጠንካራ አቋምና ፅናት የህይወት ዋጋ ከፍለው የማይደፈረውን የውጭ ጠላት ድባቅ እየመቱ የዛሬዋን ኢትዮጵያን አስረክበውናል፡፡ እኛ የጥራት መንደር አመራሮችና ሠራተኞችም በተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ትብብርና አንድነትን በማጠናከር ብሎም ፅኑ ዓላማን በማንገብ በክብር የተቀበልናትን ሀገር በልማት ወደፊት ማሻገር ይኖርብናል ብለዋል፡፡
እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ ዘመኑ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጊዜ መሆኑን ተገንዝበን ያለንን እውቀት፣ ጉልበትና አቅም ተጠቅመን ለመልካም ውጤት መትጋትና ሀገርን ከፍ ወዳለ የእድገት ደረጃ ማሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ኃለፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመርና ሠንደቅ አላማ በመስቀል ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia
Website: www.ethiometrology.gov.et
Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute
YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology